በ2017 በጀት ዓመት የሀገርና የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

You are currently viewing በ2017 በጀት ዓመት የሀገርና የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን አቶ አደም ፋራህ ገለጹ

AMN ነሐሴ 12/2017

በ2017 በጀት ዓመት የሀገርና የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ እና የ2018 መነሻ እቅድ ላይ ያተኮረ መድረክ አካሂዷል።

በዚህ ወቅት አቶ አደም እንዳሉት፤ የፓርቲው አመራርና አባላት በተባበረ ክንድ ተናበው መትጋት በመቻላችን በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

በ2017 በጀት ዓመት በፓርቲው በተሠሩ ሥራዎች የውስጠ ፓርቲ ጥንካሬ መጎልበቱን፣ ስትራቴጂያዊ ትብብር እና አጋርነት መረጋገጡን እና የሀገርና የሕዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉንም ጠቅሰዋል።

በበጀት ዓመቱ ሕዝብ በልማት ተጠቃሚ እንዲሆን የተሠሩ ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩም ተናግረዋል።

በተጨማሪም በሰላምና መረጋጋት ረገድ የተሠሩ ሥራዎች በሀገር ደረጃ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን አስችለዋል ብለዋል።

በ2018 የበጀት ዓመት ሁሉም አመራርና አባላት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በትጋት መሥራት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review