በከተማ ደረጃ በወርሃ ሃምሌ የተሰበሰበው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ50 በመቶ ብልጫ እንዳለው የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በሃምሌ ወር በከተማ ደረጃ 26.54 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ዓቅዶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡
በዕቅዱ መሰረትም 26.24 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 98.8 በመቶ ያከናወነ ሲሆን፣ ከተሰበሰበው ገቢ፣ በገቢዎች ቢሮ ደረጃ ለመሰብሰብ ከታቀደው 21.8 ቢሊየን ብር ውስጥ 22.56 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 103 በመቶ ማከናወኑን የቢሮው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል በላኩት መረጃ መረዳት ተችሏል፡፡
በሃምሌ ወር እንደ ከተማ የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር 8.7 ቢሊየን ብር ወይንም 50 በመቶ ዕድገት እንዳለው በመረጃው ተመላክቷል፡፡
በዘንድሮው በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማ ደረጃ 350 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ዓቅዶ ወደ ስራ የተገባ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 256 ቢሊየን ብር በገቢዎች ቢሮ ለመሰብሰብ የታቀደ ነው፡፡
በያለው ጌታነህ