የስፔን ላሊጋ የ2025/26 የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት መርሃግብር ዛሬም ቀጥሎ ሪያል ማድሪድ ከ ኦሳሱና ይጫወታል።
ሪያል ማድሪድን ይዞ በዓለም የክለቦች ዋንጫ የተሳተፈው ስፔናዊው አሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ የመጀመሪያ የላሊጋ ጨዋታውን ይመራል።
በማድሪድ በኩል በእንግሊዝ ሃያላን ክለቦች የሚፈለገው ሮድሪጎ የስብስቡ አካል ሆኗል።
የ24 ዓመቱ ብራዚላዊ በዓለም የክለቦች ዋንጫ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ መጫወቱ ክለቡን እንዲለቅ ይገፋዋል የሚሉ መረጃዎች በስፋት ሲወጡ ነበር።
በአርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ የሚፈለገው ሮድሪጎ የእቅዱ አካል እንደሆነ ዣቪ አሎንሶ ከጨዋታው በፊት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግሯል።
የትከሻ ቀዶ ህክምና ያደረገው እንግሊዛዊው አማካይ ጁድ ቤሊንግሃም በጨዋታው አይሳተፍም።
በሳንቲያጎ ቤርናቢዩ የሚደረገው ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ይጀምራል።
በሸዋንግዛው ግርማ