የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናለድ ትራምፕ ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ፣ በቀጣይ ከሩሲየ አቻችቸው ጋር ለመነጋጋር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ነበር፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር ያደረጉት ውይይት ከተጠናቀቅ በኋላ የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በስልክ ማነጋገራቸውም ይታወሳል፡፡
ፑቲን ከዘለንስኪ ጋር ተገናኝተው ለመምከር ፈቃደኝነታቸውን እንደገለፁላቸው አስታውቀዋል፡፡
በነጩ ቤተ መንግስት የተካሄደው እና ትራምፕ፣ ዜለንስኪ እና የአውሮፓ መሪዎች የተሳተፉበት ውይይት ፍሬያማ እንደነበር መግላጸቸውም ይታወቃል፡፡
በፕሬዚዳንት ትራምፕ አመቻችነት ለመወያየት ዝግጁ የሆኑት ፑቲን እና ዘለንስኪ በሀንጋሪ ቡዳፔስት ሊገናኙ እንደሚችሉ የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል፡፡
ማሬ ቃጦ