የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

AMN- ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት (JETRO) በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የኢትዮዽያ አየር መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ያደቻ ከጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት ሊቀመበር ኢሺጉሮ ኖሪሂኮ ጋር በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።

የተፈረመው መግባቢያ ስምምነት አፍሪካ ያለውን የካርጎ ኔትዎርክ በመጠቀም የጃፓን የንግድ ማህበረሰብ የሚያመርታቸውን ምርቶች በአፍሪካ ለማሰራጨት፣ የአፍሪካ ምርቶችን ወደ ጃፓን ኤክስፖርት ለማድረግ እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኘውን ካርጎ በጋራ ለማልማት የሚያስችል ነው።

ስነ-ስርዓቱ የተካሄደው በጃፓን በሚካሄደው የTICAD-9 የመሪዎች ጉባዔ የሚሳተፈውን የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን የመሩት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በተገኙበት ነው።

በስነ-ስርአቱ ላይ አቶ መላኩ አለበል፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ተደራሽነቱን እያሰፋ እንደሚገኝ ገልጸው፣ በዛሬው ቀን ከጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅት ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናከረው ገልፀዋል።

በጃፓን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ዳባ ደበሌ፤ የኢትዮጵያ እና ጃፓን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከጊዜ ወደጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱን በመግለጽ፤ ስምምነቱ የጎላ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ አየር መንገዱ አፍሪካን ከጃፓን ጋር ለማስተሳሰር እያከናወነ ያለውን ስራ የበለጠ እንደሚያጠናክር መገለፁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review