የ2025 የዳይመንድ ሊግ ሊጠናቀቅ በሦስት ከተሞች የሚደረጉ ውድድሮች ቀርተዋል ፡፡ 13ኛ ዙሩ ዛሬ በስዊዘርላንድ ሎዛን ከተማ ይደረጋል ፡፡ በዚህ ዙር ኢትዮጵያውያን አትሎቶች በሁለት ርቀቶች ይወዳደራሉ፡፡
በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል አራት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሲምቦ አለማየሁ ጥሩ ተፎካካሪ ትሆናለች ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
መሰረት የሻነህ ፣ ወሰኔ አሰፋ እና አለምናት ዋለ በርቀቱ የሚሳተፉ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው ፡፡
በ5000 ሜትር ወንዶች ሀጎስ ገ/ሕይወት የአሸናፊነት ግምት ሲሰጠው ፤ ጥላሁን ሃይሌ ፣ ሳሙኤል ተፈራ ፣ መዝገቡ ስሜ እና አብዲሳ ፈይሳም ይሳተፋሉ ፡፡
የዘንድሮ ዳይመንድ ሊግ በቀጣይ በብራስልስ እና ዙሪክ ተደርጎ በይፋ ይጠናቀቃል ፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ