ችግሮችን በምክክር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ምሁራን ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸዉ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ችግሮችን በምክክር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ምሁራን ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸዉ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN ነሐሴ 14/2017

ችግሮችን በምክክር በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ምሁራን ተሳትፏቸውን ይበልጥ በማጠናከር ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) ገለጹ።

ኮሚሽኑ በአማራ ክልል ከሚገኙ የዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን ጋር በምክክሩ አስፈላጊነት፣ እስካሁን በተገኙ ስኬቶችና በቀጣይ ስራዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ(ዶ/ር) እንደተናገሩት፥ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት ሀገር ለመገንባት ምክክርን ባህል በማድረግ ችግሮችን በጋራ መፍታት ያስፈልጋል።

ለዚህም በሃገራዊ ምክክር የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፍታት ህዝቡ በአብሮነት፣በፍቅርና በመተሳሰብ እንዲኖር የሚያስችል ምዕራፍ መከፈቱን ገልጸዋል።

ችግሮችን በምክክር ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ምሁራን በእውቀት የታገዙ ምርምሮችን በማካሄድና የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በማምጣት ተሳትፏቸውን ይበልጥ አጠናክረው ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

ምሁራን በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የሚችሉትን ሁሉ ማበርከት አለባቸው ብለዋል።

አባቶቻችን በየዘመናቱ ባካሄዱት ተጋድሎ ዳር ድንበሯ የተከበረ ሀገር አስረክበውናል ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ሰላሟ የሰፈነና ያደገች ሀገር እንድትኖረን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምሁራን የምክክር ኮሚሽኑን ዓላማ በማስረዳት የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ የማስቻል ስራ ማከናወን እንዳለባቸውም አንስተዋል።

የውይይት መድረኩ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ተመልክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review