በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን በመዘርጋት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለጹ

You are currently viewing በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን በመዘርጋት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለጹ

AMN – ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም

በ2018 ዓ.ም በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን በመዘርጋት ከእንግልትና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያና አሰራር ዙሪያ ከህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።

የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በማበልጸግ የከተማዋን የተሟላ ሰላም ለማስጠበቅ ከተሰሩ ስራዎች ባሻገር፣ ከቢሮ እስከ ወረዳ ያሉ የጸጥታ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በመደገፍ አበረታች ለውጦች መገኘታቸውን የቢሮ ኃላፊዋ ገልጸዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ሁሉን አቀፍ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ስራዎች እቅድ ውስጥ በ2017 በጀት ዓመት ከህብረተሰቡ የተነሱ ሀሳቦችን በማካተት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

በተለይ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ ያልተቀረፉ ብልሹ አሰራሮችንና ሙሰኝነትን ለማስቀረት አሰራሮችን በቴክኖሎጂ የመደገፍ ስራ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በተለይም ከኩነት ምዝገባ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ ባለበት ሆኖ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል መተግበሪያን በማበልጸግ ወደ ስራ ማስገባቱን ተናግረዋል።

ከሰው ሀብት አስተዳደር፣ ከሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ስራ ጋር ተያይዞ ያሉ ስራዎችንም ለማከናወን የዘመነ አሰራር ተዘርግቷል ብለዋል።

በ2017 ዓ.ም ለተመዘገቡ ስኬቶች፣ የህብረተሰቡ ተሳትፎ የማይተካ ሚና ነበረው ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ፣ አሁንም በእቅዱ መካተት አለባቸው ተብለው ከህብረተሰቡ የሚነሱ ሀሳቦን እንደ ግብአት በመውሰድ፣ ሰላሟ የተጠበቀ ከተማ ለመፍጠር ከህዝብና ከተቋማት ጋር ያሉ ቅንጅታዊ አሰራሮች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ አረጋግጠዋል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review