AMN ነሀሴ 14 /2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አራተኛው “የመደመር መንግሥት” መጽሐፍ አገር በቀል መሆኑን ያስረዱ ሲሆን ፣መደመር በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኝ እሳቤ መሆኑን ገልፀዋል።
ተመሳሳይ እሳቤዎች በሌሎች አከባቢዎች ሊኖር እንደሚችሉ ገልፀው፣ የእኛ መደመር አገር በቀል እና ኢትዮጵያ ውስጥ በስፋት የሚገኝ እሳቤ መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ እሳቤው ኢትዮጰያ ውስጥ ሳይኖር ቀርቶ ከውጭ የገባ አይደለም ያሉ ሲሆን እሳቤውን ኢትዮጰያውያን ኖረውበታል፣ ሰርተውበታል፣ አትርፈውበታል እንደ አገርም ፀንተውበታል በማለት የመደመር እሳቤ ጥንታዊነትን አስረድተዋል።
መደመር በማህበረሰብ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ለኢትዮጰያውያን አገልግሏል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እሳቤው ስርዓታዊ መልስ አልተሰጠውም እንጂ አልነበረም ማለት እንዳልሆነ ገልፀዋል። የመደመር እሳቤ በተለያየ መንገድ ሲተገበር መቆየቱንም ተናግረዋል።
”ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ” አባባልን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ድር ከአንበሳ አንፃር ደካማ ቢሆንም ፣ቢያብር ግን አንበሳን ያስራል። መደመርም የዚህ ብሂል ነፀብራቅ ነው ብለዋል።
በእያንዳንዱ ማህበረሰብ ውስጥ መደመር በአባባሎቻችን፣ በንግግሮቻችን፣ በልምምዶቻችን፣ የኖርንበት የሰራንበት የፀናንበት እሳቤ ነው በማለት አስረድተዋል።
ነገር ግን ይህንን የመደመር እሳቤ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ቀመር አድርገን አላወጣነውም ሲሉ ተናግረዋል።
መደመር አገር በቀል እሳቤ የሚያደርገው ሁኔታዎችን የሚተነትንበት የመፍትሄ አማራጭ የሚያመላክበት ፤ግቡን ያስቀመጠበት፤ ሂደቱትን ያብራራበት መንገዶች በሌሎች አገሮች የማይገኝ በመሆኑ እሳቤው አገር በቀል ያስብለዋል በማለት አስረድተዋል ።
በሔለን ተስፍዬ