ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በሃረሪ ክልል በስራ ላይ የሚገኙ ማስ ኢንጅነሪንግ ኢንተርፕራይዝ እና አዱ የዱቄት ፋብሪካን መጎብኘታቸዉን ገለጹ።
አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት በሐረሪ ክልል እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ሀገራዊ ግቦቻችንን የማሳካት ትግበራችን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ለመሸጋገሩ አብነቶች ናቸው ብለዋል።
ዛሬ በክልሉ በስራ ላይ የሚገኙ ማስ ኢንጅነሪንግ ኢንተርፕራይዝ እና አዱ የዱቄት ፋብሪካን ጎብኝተናል፡፡
የብረታ ብረት ፋብሪካው በከተማ እንዲሁም በአጎራባች ከተሞች እየተሰሩ ለሚገኙ የኮሪደር ልማት እና የከተማ ማስዋብ ስራዎች ትልቅ ሚናን እየተወጣ ይገኛል፡፡ የዱቄት ፋብሪካውም የስንዴና የቦቆሎ ዱቄትን በማምረት በጅምላና በችርቻሮ ለህዝቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ አይተናል ብለዋል።
በሌላ በኩል የእንቁላል መንደርን እና የወተት መንደርንም ተዘዋውረን የተመለከትን ሲሆን የሌማት ትሩፋት በምግብ ራስን ለመቻል ለምናደርገው ጥረት ሚናው ላቅ ያለ ለመሆኑ ማሳያዎች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።