በቀጣይ በሀገሪቱ የሚካሄዱ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶች ጋር በተያያዘ ያለውን ዝግጅት የፀጥታ መዋቅሩ ገመገመ

You are currently viewing በቀጣይ በሀገሪቱ የሚካሄዱ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶች ጋር በተያያዘ ያለውን ዝግጅት የፀጥታ መዋቅሩ ገመገመ

AMN ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም

በቀጣይ በሀገሪቱ የሚካሄዱ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረኮች ጋር በተያያዘ ያለውን ዝግጅት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የፀጥታ መዋቅሩ ገምግሟል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በተገኙበት በተደረገው ግምገማ በአጠቃላይ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ መሆኑ ተገምግሟል፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሰፊ ቁጥር ያለው በቴክኖሎጂ የታገዘ የሰለጠነ የሰው ኃይል በዚህ ሥራ ላይ ስምሪት እንደሚያደርግ ተገልጻል።

ሕብረተሰቡ እስከአሁን ድረስ ከፀጥታና ደኅንነት መዋቅሩ ጋር ተቀናጅቶ የከተማዋን ሰላምና ደኅንነት በማስጠበቅ ከፍተኛ ኃላፊነት ወስዶ ትላልቅ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ በግምገማው ላይ ተነስቷል።

ተቋሚ ለኤ ኤም ኤን በላከው መግለጫ ሕብረተሰቡ በቀጣይም ይህንኑን አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታ መዋቅሩ ጥሪ አቅርቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review