ኢትዮጵያ 41ኛውን የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ዓመታዊ ጉባኤ ልታስተናግድ ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ 41ኛውን የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ዓመታዊ ጉባኤ ልታስተናግድ ነው

AMN- ነሀሴ 15/2017

ኢትዮጵያ 41ኛውን የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ዓመታዊ ጉባኤ ከነሀሴ 19 እስከ 23/2017 ዓ.ም ድረሽ እንደምታስተናግድ ተገለጸ፡፡

ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው 41ኛውን የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ዓመታዊ ጉባኤ ዝግጅት መጠናቀቁን ተከትሎ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

በግለጫውን የሰጡት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተርና የማህበሩ ምክትል ሊቀመንበር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ በትምህርት ስርዓቷ ላይ ባደረገችው ለውጥና ውጤት ኮንፈረንሱን እንድታዘጋጅ መመረጧን ተናግረዋል።

የጉባኤው ዋና ዓላማ ተሞክሮዎችን መለዋወጥና በአባል ሀገራቱ መካከል ያለውን የትምህርት ስርዓት ማጠናከር ስለመሆኑም ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለፁት።

በኮንፈረንሱ ከ30 ሀገራት የተውጣጡ ከ500 በላይ ሉዑካን የሚሳተፍ ሲሆን፤ ከ120 በላይ የምርምር ወረቀቶች ይቀርባሉ ተብሏል።

በኮንፈረንሱ የትምህርት ምዘናን ፍትሀዊነትንና ሁለንተናዊነት ላይ፤ የትምህርት ምዘናው በዲጂታል መንገድ እንዲካሄድ ለማስቻል፣ የትምህርት ምዘና ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ትስስር ለማድረግና የምዘና ጥናቶችን ተንትኖ መጠቀም ላይ በጋራ እንደሚመከር በመግለጫው ተመላክቷል።

41ኛው የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ዓመታዊ ጉባኤ ከነሀሴ 19 እስከ 23-2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተመላክቷል።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review