ሩሲያ በዩክሬን ላይ የድሮን እና ሚሳኤል ጥቃቶችን ፈፀመች

You are currently viewing ሩሲያ በዩክሬን ላይ የድሮን እና ሚሳኤል ጥቃቶችን ፈፀመች

AMN- ነሀሴ 15/2017

ሩሲያ በሳምንቱ ከፍተኛ የተባለለትን ጥቃት በዩክሬን ላይ መፈጸሟን የዩክሬን ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ሩሲያ 574 ደሮኖችን እና 40 ሚሳኤሎችን ነው በዩክሬን ላይ የሰነዘረችው፡፡በጥቃቱም የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 15 ሰዎች ቆስለዋል፡፡

ጥቃቱ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራም በሀገራቱ መካከል ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ለማበጀት በሚጥሩበት ወቅት ላይ የተፈፀመ ነው፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከሩሲያው አቻቸው ፑቲን ጋር ድርድር ለማድረግ ፈቃደኛ በሆኑበት ወቅት ላይ የተከሰተ መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን ቀላል እንደማያደርገው ተሰግቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review