ገደላማው ቤተ-መፃህፍት

You are currently viewing ገደላማው ቤተ-መፃህፍት

AMN – ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም

በፀጥተኛዋ መንደር ሚያንሁዋ በተራራዎች መሃል ተደብቋል።

በቻይና ጉዋንዢ ግዛት እንደሌላው ያልሆነ ቤተ መፃህፍት ይገኛል።

በገደላማው ስፍራ በተራራው ወገብ ላይ እንደ መቀነት የተሰራው የሚያንሁዋ ቤተ መፃህፍት፣ እውነት በማይመስል መልኩ ስነ -ጽሁፍን ከመልከዓ ምድር ጋር በማዋሃድ ለስፍራው ልዩ ውበትን ሰጥቶታል።

ምንም እንኳን ቤተ መፃህፍት በማህበራዊ ሚዲያው ሞገድን ሲፈጥሩ እምብዛም ባይስተዋሉም፣ ይሄኛው ግን ባለንበት ዓመት ግንቦት ወር ለአገልግሎት ክፍት ከተደረገ ጊዜ ጀምሮ በቻይናዊያን ማህበራዊ ሚዲያ ስሜት ገዢ መሆን ችሏል።

የዲጂታል ምናብ ስራ የሚመስለው ይህ ቤተ መፃህፍት፣ ወደ ስፍራው ለተጓዙ ሁሉ በተፈጥሮ ውበት የታጀበ አገልግሎት ቢሰጥም፣ ወደ ስፍራው የሚያቀኑት ቱሪስቶች ቁጥር ከአንባቢያኑ ልቀዋል።

ጠባቦቹ የእንጨት መተላለፊያዎች እና የተንጠለጠሉ መፅሃፍት መደርደሪያዎቹ የገደሉን ቅርፅ ተከትለው የተዘረጉ መሆናቸው ለጎብኚዎች ተፈጥሮና ስነ-ህንፃ ተዋህደው ለማየት ቢያስችሏቸውም የከፍታ ፍራቻ ያለበት ግን አይደፍራቸውም።

በሃገሪቱ ገጠራማ ክልል የሚገኘው ቤተ-መፃህፍቱ፣ ለአካባቢው ነዋሪ ከመፅሃፍት ባለፈ የቱሪስት ፍሰትን የጨመረ ነው ሲል ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review