በምናብ ማየት መጨከን፣ መወሰንና መትጋት የወንዝ ዳርቻ ስራዎች ስኬታማነት አረጋግጧል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

You are currently viewing በምናብ ማየት መጨከን፣ መወሰንና መትጋት የወንዝ ዳርቻ ስራዎች ስኬታማነት አረጋግጧል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ
  • Post category:ልማት

AMN- ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም

የወንዝ ዳርቻ ልማት እንደ ግሪን ሌጋሲ ለመላው አፍሪካ ምሳሌና ምልክት ተደርጎ የሚወሰድ ድንቅ ውጤት የተመዘገበበት ስራ መሆኑን የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “የመደመር መንግሥት” የተሰኘውን አዲስ መጽሐፍ በተመለከተ ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።

ይህ ድንቅ ውጤት የመንግስት ምናባዊ እይታ ጥልቀት ያመላከተም ተግባር ነው ብለዋል።

በወንዝ ዳርቻ ልማት በተፈጠሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት ፡፡

የኢትዮጵያ የከተማና የገጠር ኮሪደር ልማት ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን የሚጨበጥ የሚታይ ድንቅ ስራ መሆኑንና ይህንንም ወዳጅ ሀገራት ጭምር ያረጋገጡት ስራ ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ለወንዝ ዳርቻ ስራዎች ስኬት በምናብ ማየት መጨከን፣ መወሰንና መትጋት ብሎም የበርካታ አመራሮች የይቻላል ድምር ውጤት መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱት።

“የመደመር መንግስት” መፅሐፍ የኮሪደር ልማት በአዲስ የፋይናንስ አቅም ሊከወን እንደሚችል የሚያመላክት ነው ሲሉ በቆይታቸው አብራርተዋል።

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review