አሜሪካ በቤትና የቢሮ ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች

You are currently viewing አሜሪካ በቤትና የቢሮ ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች

AMN- ነሐሴ17/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በሚቀጥሉት 50 ቀናት ውስጥ፣ ወደ አሜሪካ በሚገቡ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ እንደሚደረግ ማስታወቃቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

ትራምፕ እስከ ጥቅምት ወር ድረስ፣ ወደ አሜሪካ በሚገቡ እና ከፍተኛ ታሪፍ በሚጣልባቸው የቤትና የቢሮ እቃዎች ላይ አስተዳደራቸው ምርመራ እንዲያደርግ አቅጣጫ መስጠታቸው ተገልጿል።

ምርመራው በሚቀጥሉት 50 ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ እና ከውጭ ወደ ሀገሪቱ በሚገቡ የቤትና የቢሮ እቃዎች ላይ የሚጣለው ታሪፍ በመቶኛ መጠኑ ስንት ሊሆን ይችላል የሚለው አለመወሰኑን ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ማስፈራቸው ታውቋል።

ምርመራው የመጣው የትራምፕ አስተዳደር ከውጭ በሚገቡ እንደ መዳብ፣ ከፊል ኮረንቲ አስተላላፊዎች እና የህክምና ቁሳቁሶች ላይ ከፍተኛ ታሪፍ መጣላቸውን ተከትሎ ነው።

ትራምፕ ከቻይና እና ቬትናም በሚገቡ ዕቃዎች ላይ የታሪፍ ጭማሪ በመደረጉ፣ የቤትና የቢሮ እቃዎች ዋጋ ባለፉት ጥቂት ወራት እየጨመረ መምጣቱ ተመላክቷል።

ቻይና እና ቬትናም ባለፈው ዓመት 12 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ የቤት እቃዎችን ወደ አሜሪካ ማስገባታቸውን የአሜሪካ የንግድ ዲፓርትመንት መረጃ አመላክቷል።

ከግንቦት ወር ጀምሮ የቢሮ፣ የመዝናኛ እና ሌሎች የቤት እቃዎች ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየታቸውም ነው የተገለጸው።

በግንቦት ወር 1.5 በመቶ፣ በሰኔ 1.6 በመቶ እና በሐምሌ 1.5 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ማሳየታቸውም ተጠቁሟል።

በብርሃኑ ወርቅነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review