360 ከረባቶችን በማሰር አዲስ ክብረወሰን የሰበረችው ካናዳዊት ፖለቲከኛ

You are currently viewing 360 ከረባቶችን በማሰር አዲስ ክብረወሰን የሰበረችው ካናዳዊት ፖለቲከኛ

AMN- ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም

የፖለቲካ ህይወት በቃኝ ብላ ጡረታ ለመውጣት በዝግጅት ላይ የምትገኘው ካናዳዊት ማርዋህ ሪዝኪ፣ 360 ከረባቶችን በማሰር አዲስ የዓለም ክብረወሰን ለመስበር አንገቷን በከረባት ሞልታ ታይታለች፡፡

የኩዊቤክ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆነችው ማርዋህ ሪዝኪ በ2026 ዳግም መመረጥ እንደማትፈልግም አስታውቃለች፡፡

በካናዳ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው ኢንፎርማን በተሰኘው ተከታታይ ዝግጅት ላይ ቀርባ የሥልጣን ጊዜ ቆይታዋንም አክብራለች፡፡

በፈረንጆቹ 2023 ብራዚላዊው ዴቪድ አፓሬሲዶ ዶ ሳንቶስ አራውጆ የተባለ ግለሰብ 330 ከረባቶችን በአንገቱ ላይ በማሰር ነበር የዓለምን ክብረ ወሰን ጨብጦ የቆየው፡፡

ማርዋህ ሪዝኪ፣ በብራዚላዊው ተይዞ የቆየውን ክብረወሰን ለመሰበር የወሰነችውም ሴቶች ከወንዶች እኩል እንደሆኑና ብዙ ከረባት ማሰር እንደሚችሉ ለማሳየት ነው ስትል ተናግራለች፡፡

ሪዝኪ 330 ከረባቶችን በማሰር የቀደመው ክብረወሰን ላይ ለመድረስ 48 ደቂቃዎች ብቻ የፈጀባት ሲሆን፣ ከረባቶች ተጠምጥመውባት ፊቷ ከአንገት በላይ በጥቂቱ ብቻ ይታይ ነበር፡፡

በመጨረሻም ተጨማሪ 30 ከረባቶችን በማሰር በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ስሟን ማስፈር እንደቻለች ነው የዩፒአይ ዘገባ ያመለካተው፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review