የነቀምቴ ከተማ ቆይታዉን ያጠናቀቀዉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በአምቦ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

You are currently viewing የነቀምቴ ከተማ ቆይታዉን ያጠናቀቀዉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በአምቦ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

AMN ነሐሴ 17/2017

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የትውልዱ የጥንካሬና የህብረ ብሄራዊ አንድነት ሁነኛ ማሳያ መሆኑን የምዕራብ ሸዋ ዞን እና የአምቦ ከተማ ፖሊስ አባላት ተናገሩ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ነቀምቴ ከተማ የነበረውን ቆይታ አጠናቆ አምቦ ከተማ ሲገባ አቀባበል ተደርጎለታል።

ዋንጫው አምቦ ከተማ ሲገባም የዞኑና የከተማው ፖሊስ አባላትና ከፍተኛ አመራሮች፣ እንዲሁም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በስፍራው በመገኘት አቀባበል አድርገዋል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የምዕራብ ሸዋ ፖሊስ ጽፈት ቤት ኃላፊ ኮሚሽነር ሁንዴ በቀሌ፤ የፖሊስ አባላት ሰላም ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ለህዳሴው ግድብ የቦንድ ግዥና ሌሎችም አስፈላጊ ድጋፍና እገዛዎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

የህዳሴ ግድብ የትውልዱ የጥንካሬና የህብረ ብሄራዊ አንድነት ሁነኛ ማሳያ መሆኑን አንስተው የፖሊስ አባላቱ እገዛና ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

በአምቦ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የእቅድና በጀት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ከበደ ገላልቻ፤ የፖሊስ አባላት ለግድቡ የሚያደርጉት ድጋፍ ከጅምሩ እስካሁንም ድረስ ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል።

የግድቡ ግንባታ የእዚህ ትውልድ የጥንካሬ መገለጫ እና የህብረ ብሄራዊ አንድነት ማሳያ መሆኑን አንስተው መሰል ስኬቶችን ለማስመዝገብ የጋራ ጥረታችን መቀጠል አለበት ብለዋል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ከተገኙት የምዕራብ ሸዋ ነዋሪዎች መካከል ወጣት ጉደታ ድሪባ፤ የግድቡ ግንባታ ስኬት በቀጣይ ለሚከናወኑ ግዙፍ የልማት ስራዎችም በጥሩ ተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review