መንግስት የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገለፁ።
የቴክኖሊንክ ኮሌጅ በ2017 የትምህርት ዘመን በተለያዩ የሙያ መስኮች ያስተማራቸውን ከ1500 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።
መርሃ ግብሩ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ መንግስት የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጄና (ዶ/ር) በበኩላቸው ፣መንግስት ባለፉት የለወጥ አመታት የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ለማስፋት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ተመራቂ ተማሪዎች በተመረቁበት የሙያ መስክ ማህበረስቡን በታማኝት ማገልገል እንዳለባችውም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የቴክኖሊንክ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት አቶ ደቻሳ መርጋ፤ የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማስፋት የሁሉንም ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ተናግረዋል። ኮሌጁ የሀገርን እድገት የሚያስቀጥሉ ሙያተኞችን እያፈራ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡
የትምህረት ጥራትን እና ተደራሽነትን ለማስፋት የሁሉም ትብብር እንደሚጠይቅ የተናገሩት አቶ ደቻሳ፤ ኮሌጁ የትምህረት ጥራትን ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ተመራቂ ተማሪዎቹ በተመረቁበት የሙያ መስክ በታማኝነት እና በቅንንነት ሀገራቸውን ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውንም ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል።
በመሀመድኑር ዓሊ