የቄራዎች ድርጅት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማግኘት የሄዱ ተገልጋዮችን ገንዘብ የጠየቁ ሁለት ተጠርጣሪ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተገልጿል።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰይድ እንድሪስ ከማል እና ምክትላቸው አቶ እድሪብሳ ማሞ ገንዘብ ካላመጣችሁ አገልግሎት አታገኙም በማለት ፤ እንግልት ሲፈጠሩ ቆይተው በደረሰ ጥቆማ በዛሬው ዕለት ከተገልጋይ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
ተገልጋዮች ተከታትለዉ ለሰጡት ጥቆማ ያመሰገነዉ ጽ/ቤቱ በቀጣይም ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ትግል ሁሉም መተባበር እንደሚገባዉ ጥሪ አቅርቧል።
ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት የሙስና ተግባራትን ሲመለከት ለከንቲባ ጽ/ቤት የሙስና ወንጀል ጥቆማ ተቀባይ በመጠቆም ሙስናን የመከላከል ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ ጽ/ቤቱ ጨምሮ አሳስቧል።