የመጀመሪያው ዓለም ዓቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ በርካታ ተሳታፊዎች በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።
ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አምባሳደር ተወካይ ራሽድ አብደላ ሻይ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚዎች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም በቴምር ዘርፍ የተሰማሩ እና ከተባበሩት አረብ ኢምሬት የከሊፋ ኢንተርናሽናል አዋርድ ፎር ዴት ፓልም ኤንድ አግሪካልቸር ኢኖቬሽን፣ ከሳዑዲ እና ሌሎች አገራትም በርካቶች መሳተፋቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለሶሰት ቀናት በሚካሄደው ፌስቲቫል የተሻሻሉ የቴምር ዝርያዎች በተሞክሮነት ቀርበው የሚታዩ ሲሆን በዘርፉ ልማት የተሞክሮ ልውውጥ የሚደረግም ይሆናል።