ለ34 ሰምንታት መቆየት የቻለው ሰው ሰራሽ ኩላሊት

You are currently viewing ለ34 ሰምንታት መቆየት የቻለው ሰው ሰራሽ ኩላሊት

AMN- ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም

የሰው ልጅ ከፍተኛ ጥናት እና ምርምር ከሚያደረግባቸው ዘርፎች መካከል ገዳይ በሸታዎችን መከላከል አልያም ፈዋሽ መድሀኒቶችን መፍጠር አንዱ ነው።

በእስራኤል የሚገኝ የህክምና ተቋም በቤተ ሙከራ ለ34 ሳምንታት የቆየ ሰው ሰራሽ ኩላሊትን መፍጠር ችሏል።

ሼባ የህክምና ተቋም ከቴልአቪቭ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እያደረገ በሚገኘው ጥናት እና ምርምር በህክምናው ዘርፍ ከፍተኛ የተባለ ግኘትን አስመዝግቧል።

ይህ ሰው ሰራሸ ኩላሊት ገዳይ የሆነውን የኩላሊት ስራ ማቆም በሸታ ለመረዳት እና ፈዋሽ መድሀኒት ለመፍጠር ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርግ የሼባ የህክምና ተቋም ተመራማሪ ቤንጃሚን ዴክል ተናግረዋል።

ምርምሩ መድሀኒት ለማግኘት የሚደረገውን ጥረት በማፋጠን እገዛ ከማድረጉም በላይ ፥በጊዜ ሂደት ተፈጥሯዊውን ኩላሊት የሚተካ ሰው ሰራሸ ኩላሊትን መፍጠር የሚያስችል መሆኑም ነው የተገለጸው።

ምርምሩ ወደ ክሊኒካል ሙከራ ደረጃ ለማሸጋገር አሁንም ቀሪ ስራዎች የሚጠበቁ ሲሆን ይህን ለማድረግ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተነግሯል።

እንደ ምርምር ተቛሙ ገለጻ ከሆነ በቻይና እና በሆንግ ኮንግ የሚገኙ የመድሀኒት አምራች ኩባንያዎች ምርምሩን በገንዘብ ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል።

ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ይዞት በወጣው ዘገባ ከፍተኛ የኩላሊት ህመም ስርጭት የሚገኝባት ቻይና በአሁኑ ወቅት ከ150 ሚሊየን በላይ ኬዝ ተመዝግቦባታል።

በዳዊት በሪሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review