ሞሮኮ እና ማዳጋስካራ ለፍፃሜ ደረሱ

You are currently viewing ሞሮኮ እና ማዳጋስካራ ለፍፃሜ ደረሱ

AMN – ነሃሴ 21/2017 ዓ.ም

በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዚኒያ አዘጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የፍፃሜ ተፋላሚዎችን ለይቷል።

ትላንት ምሽት በተደረጉ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ሞሮኮ እና ማዳጋስካር ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።

ማዳጋስካር በርካቶችን ያስደነቀ ጉዞ ያደረገችውን ሱዳንን 1ለ0 በማሸነፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የፍፃሜ ተፋላሚ ሆናለች።

ሞሮኮ ሴኔጋልን ገጥማ በመለያ ምት አሸንፋለች። 120 ደቂቃው 1ለ1 በማለቁ በተሰጠ የመለያ ምት ሞሮኮ 5ለ3 መርታት ችላለች።

የሁለት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ሞሮኮ ዋንጫውን ለማንሳት የፊታችን ቅዳሜ ማዳጋስካርን በናይሮቢ የምትገጥም ይሆናል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review