የሚዲያ ባለሙያዎች መረጃን ከማስተላለፍ ባለፈ ሀገራትን ማስተሳሰር እና ማስተባበር እንደሚገባ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ

You are currently viewing የሚዲያ ባለሙያዎች መረጃን ከማስተላለፍ ባለፈ ሀገራትን ማስተሳሰር እና ማስተባበር እንደሚገባ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ

AMN – ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም

የምስራቅ አፍሪካ ሚዲያዎችና የተግባቦት ባለሙያዎች የመረጃ ማስተላለፊያ ብቻ ሳይሆኑ ሀገራቱን የማስተሳሰር፣ የማስተባበርና ከፍ ሲልም የሰላም ድልድይ ሊሆኑ እንደሚገባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል፡፡

15ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኮሙኒኬሽን ማህበር ጉባኤ በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው።

“ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ለአፍሪካዊያን ትስስር” በሚል መሪ ሃሣብ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ላይ የተገኙት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር)፣ አፍሪካ በ2063 ያስቀመጠችውን እቅድ በተለይም የሀገራት ትስስርን ማጠናከር፣ ሰላማዊ የሆነች አፍሪካን ማየት፣ ነፃ የንግድ ቀጠናን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ማድረግና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ዓለማ ለማሳካት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ትልቅ ሚናና ኃላፊነት እንዳለው አንስተዋል፡፡

ስለሆነም በተለይ የሚዲያዎችና የተግባቦት ባለሙያዎች የመረጃ ማስተላለፊያ ብቻ ሳይሆኑ የአፍሪካ ሀገራትን የማስተሳሰር፣ የማስተባበርና ከፍ ሲልም የሰላም ድልድይ ሊሆኑ እንደሚገባ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር)፣ ጨምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሳሙዔል ክፍሌ (ዶ/ር)፣ የምስራቅ አፍሪካ ኮሙኒኬሽን ማህበር ፕሬዚዳንት ማርጋሬት ጁኮ (ፕ/ር) እንዲሁም ከአባል ሀገራቱ የተውጣጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ ጋዜጠኞች፣ ተመራማሪዎች እና አጋር አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በአንዋር አሕመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review