ቼልሲ የማንችስተር ዩናይትዱን የመስመር ተጫዋች አሌሃንድሮ ጋርናቾን ለማስፈረም ተስማምቷል።
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ለ21 ዓመቱ አርጀንቲናዊ እስከ 40 ሚሊየን ፓውንድ ለማንችስተር ዩናይትድ ይከፍላል።
ተጫዋቹ ነገ የህክምና ምርመራውን ለማድረግ ወደ ለንደን እንደሚያቀና የስካይ ስፖርት ዘገባ ጠቁሟል።
የሰባት ዓመት ውልም ይፈርማል ተብሎ ይጠበቃል። ቼልሲ ተጫዋቹን የመሸጥ እቅድ ሲኖረው ከሽያጩ ትርፍ 10 በመቶውን ለዩናይትድ ለመስጠትም ተስማምቷል።
ጋርናቾ በ16 ዓመቱ ነበር ከአትሌቲኮ ማድሪድ የዩናይትድን አካዳሚ የተቀላቀለው።
በሸዋንግዛው ግርማ