አፍሪካውያን የሉዓላዊነታችን፣ የሀብታችንና የዕድገታችን ፀር የሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ልንከላከል እንደሚገባ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

You are currently viewing አፍሪካውያን የሉዓላዊነታችን፣ የሀብታችንና የዕድገታችን ፀር የሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ልንከላከል እንደሚገባ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

AMN – ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም

አፍሪካውያን የሉዓላዊነታችን፣ የሀብታችንና የዕድገታችን ፀር የሆኑ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ልንከላከል እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ 25ኛውን የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ ወንጀልን የመከላከል ቡድን (ESAAMLG) ቀጣናዊ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባን በውቧ መዲናችን በይፋ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

አፍሪካ በፍጥነት በሚለዋወጡ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በህገወጥ መንገድ የተገኘ የገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ የማቅረብ፣ ሽብርን በገንዘብ የመደገፍ እና በሌሎች ወንጀሎች እየተፈተነች ነው ሲሉም ገልፀዋል።

እነዚህ ወንጀሎች የዜጎቻችንን መሰረታዊ ጥቅሞች የሚነጥቁ፣ አህጉራዊ መሻታችንን የሚያሰናክሉ፣ እድገታችንን የሚያዳክሙና ድንበር ዘለል በመሆናቸው የትኛውም ሀገር ብቻውን ሊከላከላቸው አይችልም ብለዋል።

በመሆኑም እርምጃችን የወንጀሎችን ተለዋዋጭነት የሚመጥን፣ ጠንካራ፣ የተቀናጀ፣ በመረጃ ልውውጥና በትብብር ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ይህንን የሀገርና የህዝብ ጥቅም ፀር የሆነ አደጋ ለመከላከል ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁማ እየሠራች ሲሆን ከህዝባችን፣ ከሌሎች ሀገራትና ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review