ዛሬም የመላው ሕዝባችን ፍላጎት ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት መላክና የተማረን ትውልድ ማፍራት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ሕዝባችን የትምህርትን ጥቅም ካወቀ ሺ ዘመናት አልፈዋል ብለዋል።
ለዚህም ነው የመድረሳና የአብነት ትምህርትን ሲያስፋፋ የኖረው በማለትም አክለዋል።
ዛሬም የመላው ሕዝባችን ፍላጎት ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት መላክና የተማረን ትውልድ ማፍራት ነው በማለት ገልጸዋል።
አንዳንዶች እነርሱ ከዕውቀት ነጻ ሆነው ትውልድም ከዕውቀት ነጻ እንዲሆን ሲታትሩ ማየት ያማል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በሠለጠነ ሀገር ተቀምጦ ትምህርትን እንደመቃወም ያለ ምን አለመማር አለ? ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡