ኒኮላስ ጃክሰን ወደ ባየርን ሙኒክ ለማቅናት ተስማማ

You are currently viewing ኒኮላስ ጃክሰን ወደ ባየርን ሙኒክ ለማቅናት ተስማማ

AMN – ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም

ባየርን ሙኒክ የቼልሲውን አጥቂ ኒኮላስ ጃክሰንን ለማስፈረም ተስማምቷል።

የጀርመኑ ክለብ ተጫዋቹን በአንድ ዓመት የውሰት ውል ያስፈርማል። በብቃቱ ከተደሰተ ዝውውሩን ቋሚ የማድረግ አማራጭም አለው። ባየርን ሙኒክ ለአንድ ዓመት ውሰቱ ብቻ 15 ሚሊየን ዩሮ እንደሚከፍል ጋርዲያን ዘግቧል። ሙኒክ የሴኔጋላዊውን አጥቂ ውል ቋሚ ማድረግ ከፈለገ ደግሞ 65 ሚሊየን ዩሮ ይከፍላል።

ዛሬ ወደ ጀርመን ያቀናል ተብሎ የሚጠበቀው ጃክሰን ዝውውሩን ነገ ያጠናቅቃል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review