ለአዲስ አበባ ሰላም የፀጥታ ተቋማት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለፁ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2017 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ላይ የፀጥታ ተቋማት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የምስጋናና የእውቅና መርሀ ግብር እያካሄደ ይገኛል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፤ ለአዲስ አበባ ሰላም የፀጥታ ተቋማት ቅንጅትና ተናቦ መስራት ወሳኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ በ 2017 በጀት ዓመት ከ150 በላይ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ጉባኤዎች እንዲሁም የተለያዮ ሀይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት በሰላም የመከበራቸው ምክንያት የፀጥታ አካላት በቅንጅት መስራት ነው ብለዋል።
ከዚህ ባሻገር አሁን ያለው የአዲስ አበባ ሰላም ሁሌም ቀጣይ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት የሚሰሩትን ስራ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ወ/ሮ ሊዲያ አሳስበዋል።
እውቅና የተሰጣቸው ተቋማትም የቅንጅት ስራውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በንጉሱ በቃሉ