ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጪው ዘመን ከዓለም ኃያላን ተርታ የምትሰለፍ ብርቱ ሀገር በደምና በላብ እንገነባለን ሲሉ ገለጹ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጪው ዘመን ከዓለም ኃያላን ተርታ የምትሰለፍ ብርቱ ሀገር በደምና በላብ እንገነባለን ሲሉ ገለጹ

AMN ጳጉሜን 1/2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመጪው ዘመን ከዓለም ኃያላን ተርታ የምትሰለፍ ብርቱ ሀገር በደምና በላብ እንገነባለን ሲሉ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ የጽናት ቀን : ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር ሚል ሃሳብ ባሰፈሩት መልዕክት ኢትዮጵያ ብልጽግናዋን የምታረጋግጠው መሠረቷን ለማጽናት በሚችሉ ብርቱ እጆች ነው ብለዋል።

በሁሉም ዘርፎች በምናደርገው ተጋድሎ የኢትዮጵያን መሠረት እናጸናለን፡፡b ለማናቸውም ችግሮች የማትበገር፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል የምትቀይር፣ በመጪው ዘመንም ከዓለም ኃያላን ተርታ የምትሰለፍ ብርቱ ሀገር በደምና በላብ እንገነባለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review