የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ለምረቃ በመብቃቱ ደስታቸዉን እየገለጹ ነዉ

You are currently viewing የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ለምረቃ በመብቃቱ ደስታቸዉን እየገለጹ ነዉ
  • Post category:ልማት

AMN ጳጉሜ 3/2017

የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለምረቃ በመብቃቱ ደስታቸዉን እየገለጹ ነዉ ፡፡

የአጋሮ ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቦርቶላ አለማየሁ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደተናገሩት የከተማዋ ነዋሪዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለምረቃ በመብቃቱ የተሰማቸዉን ደስታ በምሽት አደባባይ በመዉጣት ጭምር በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡

የከተማዋ ነዋሪዎች ግድቡን ለምረቃ ያበቁትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)ና የለዉጡን መንግስት በመደገፍ አደባባይ መዉጣታቸዉን ገልጸዋል፡፡

ህዳሴዉ የህብረብሄራዊ አንድነታችን መገለጫ ነዉ ያሉት ነዋሪዎች ግድቡ በርካታ ዉጣ ዉረዶችን አልፎ ለምረቃ በመብቃቱ ተደስድተናል ብለዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review