ቁጭት የወለደው የኢትዮጵያውያን አንድነት ድል ብስራት የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ምረቃ የዋዜማ ዝግጅት በጉባ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባ ተራሮች የኢትዮጵያውያን ጽናት ተምሳሌት የሆነው የታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ምረቃ ሊበስር ሰአታት ቀርተዉታል።
የጎበጠው የሚቃናበት ዜጎች በአለም አደባባይ ዳግም አንገታቸውን ቀና አድርገው የሚመሰክሩለት ህያው ሀውልት ለውጤት መብቃት ለብዙዎቹ የአፍሪካ ሀገራት የተምሳሌትነት ማህተም ያስቀመጠ ሆኗል ።
በርካታ ውጫዊ እና ውስጣዊ ፈተናዎችን አልፎ በኢትዮጵያውያን ህብረት እና ቁርጠኝነት ለምረቃ የበቃው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ምረቃ የዋዜማ መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ን የደስታ እንባ አስነብቷል።
በመርሐ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች ተገኝተዋል፡፡
የምረቃ ዋዜማዉ በድሮን ትርዒትና በሌሎች ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ።
በዳዊት በሪሁን