ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአባይ ልጆችን አንድ የሚያደርግ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ

You are currently viewing ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአባይ ልጆችን አንድ የሚያደርግ መሆኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ

AMN ጳጉሜን 4/2017

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአባል ልጆችን በአንድ ጥላ ስር የሚያሰባስብ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

ፕሬዝዳንት ታዬ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን የማደግ መሻት በላባቸው፣ በእንባቸው፣ በደማቸው እና በክብራቸው ያሳኩት ታላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ህዳሴ ግድብ የአባይ ልጆችን አንድ የሚያደርግ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ግድቡ የኢትዮጵያ የቀጣይ ጊዜ ታላላቅ ስኬቶች ጅማሮ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

#Ethiopia

# Dam

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review