ኢትዮጵያ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኑክሌር ማብላያ ስራ በቅርቡ ትጀምራለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ኢትዮጵያ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኑክሌር ማብላያ ስራ በቅርቡ ትጀምራለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN – ጳጉሜን 4/2017 ዓ.ም

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃ ስነ ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ፤የአፍሪካ መሪዎችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በጉባ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ግድቡን ከአፍሪካ መሪዎች ጋራ የመረቁት ሲሆን ለመላዉ ኢትዮጵያዊያንና ጥቁር አፍሪካዊያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸዉ የህዳሴ ግድብን የሚስተካከል ለሠላማዊ ዓላማ የሚውል የኑክሌር ማብላያ ስራ በቅርቡ እንደሚጀመር ገልጸዋል፡፡

በጉባ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ታሪክ ሰምተናል፤ታሪክ አይተናል፤ታሪክ ተምረናል ዛሬ ፈጣሪ የመረጠዉ ትዉልድ መሆን ስለቻልን ታሪክ ሰርተን ታሪክ ላይ ቆመን ለማዉራት በቅተናል ሲሉ ተናግረዋል፡:

የትላንትናውን ታሪክ በመናገር ጊዜ አናባክንም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የህዳሴን ፋይል በመዝጋት በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ሌሎች በርካታ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል፡፡

የህዳሴ ግድብን የሚስተካከል ለሠላማዊ ዓላማ የሚውል የኑክሌር ማብላያ ስራ እንደሚጀመር የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአፍሪካ ግዙፍ የአየር መንገድ ግንባታ ስራም እንደሚከናወን ገልፀዋል፡፡

በጥቂት ሳምንታት የነዳጅ ፋብሪካ ምረቃ በማካሄድ፤ በዕለቱ አስር እጥፍ የሚሆነው 2ኛው የጋዝ ፋብሪካ ግንባታን በማስጀመር የነዳጅ ባለቤት የመሆን የዘመናት ህልማችን እውን የሚሆነበት የነዳጅ ማጣሪያ ስራ ይጀመራል ብለዋል።

እንዲህም በቅርቡ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ስራ፤ በቀጣይ አምስት አመት 1.5 ሚሊየን ቤቶች ግንባታ፤ በድምሩ ከ30 ቢሊየን በላይ ዶላር ወጪ የሚጠይቁ አፍሪካውያንን ቀና የሚያደርጉ የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያበስሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ይሰራሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሚካኤል ሕሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review