የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአድዋ ድልን የሚያስታውስ ታሪካዊ ምህንድስና መሆኑን የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሌይ ገለጹ

You are currently viewing የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአድዋ ድልን የሚያስታውስ ታሪካዊ ምህንድስና መሆኑን የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሌይ ገለጹ

AMN ጳጉሜን 4/2017

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፕሮጀክት ባለፈ የአድዋ ድልን የሚያስታውስ ታሪካዊ የምህንድስና ውጤት ነው ሲሉ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አሞር ሞትሌይ ገለጹ።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተመርቋል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር አሞር ሞትሌይ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት በውሃ የመጠቀም እና የኢነርጂን ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ለቀጣናው ሀገራት እና ለአፍሪካ ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል።

ለቀጣናው ሀገራት ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግና ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለውም ነው የተናገሩት። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በታሪኳ ኩሩ ለሆነችው እና ለኩሩው የኢትዮጵያ ህዝብ የስኬቶች ጅማሮ ነው ብለዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለዘመናት ኢትዮጵያን ለመጣል የተደረጉ ሁሉንም ጥረቶች በፅናት በመመከት ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች አካል መሆኑን ተናግረዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን የነገ ብርሃናቸውን ለማየት የየአቅማቸውን በማጣውት በአይበገሬነትና በጽናት የገነቡት ፕሮጀክት ነው ሲሉም አክለዋል። ግድቡ አፍሪካውያንና ዘርዓ አፍሪካውያን ከተጋን ማሳካት የማንችለው ነገር እንደሌለ ማሳያ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ።

በባርቤዶስ፣ በካሪቢያን ማህበረሰብ እና በአፍሪካውያን ስም ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በግድቡ አይናችንን እንድንገልጥ እና ያለንን ሀብቶች አውቀን እንድንጠቀም አንቅታችሁናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሯ በንግግራቸው።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በጋራ ከሰራን የትኛውንም ነገር ማሳካት እንደሚቻል የሚያሳይ ህያው ምስክር ሰው ሲሉም ተናግረዋል። ሁላችንም በጋራ እና በአንድነት በመቆም ህዝባችንን ለመቀየር እና መጻኢ ጊዜያችንን ብሩህ ለማድረግ እንስራ ሲሉም ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review