የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጎለብት መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አስታወቀ።
ኢጋድ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ቀጣናዊ ትብብርን የሚያሳኩ ፕሮጀክቶችን እንደሚደግፍም ገልጿል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተመርቋል።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።
ኢጋድ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፏል።
የዋና ፀሐፊው ቃል አቀባይ ፔሻንስ ንያንጌ ህዳሴ ግድብ የአይበገሬነት፣ የኢኖቬሽንና የአፍሪካ የዘላቂ ልማት የጋራ ራዕይ ምልክት መሆኑን መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢጋድ እንደ ህዳሴ ግድብ ያሉ የአባል ሀገራትን ቀጣናዊ ትስስር፣ ትብብር፣ የኢኮኖሚ አቅም እና መጻኢውን ጊዜ የብልጽግና የሚያደርጉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን እንደሚደግፍ አመልክተዋል።