በአዲስ አበባ ከተማ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምኑና የሚያቀላጥፋ የራስ አቅም ቴክኖሎጂዎችን የማልማት ስራን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀንጥራር አባይ ተናግረዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በራስ አቅምና ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር ያለማቸውን 19 ቴክኖሎጂዎችን አስመርቋል።
የለሙት ቴክኖሎጂዎች በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በቤቶች የጨረታ እና የምደባ ስርዓት፣ በጤና፣ በቱሪዝምና በሌሎች ዘርፎች አገልግሎትን የሚያዘምኑና ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ አስተዳደሩን ከተጨማሪ ወጪ የሚያድኑ ስለመሆናቸው ተመላክቷል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጀንጥራር አባይ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምኑና የሚያቀላጥፉ የራስ አቅም ቴክኖሎጂዎችን የማልማት ስራን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በመድረኩ ቴክኖሎጂ ያለሙ ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በአንዋር አህመድ