ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ኅብረት ምሳሌ መሆኑን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባዔ ገለፀ

You are currently viewing ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ኅብረት ምሳሌ መሆኑን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባዔ ገለፀ
  • Post category:ልማት

AMN – ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባዔ የኢትዮጵያውያን ኅብረት ምሳሌ በሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ምረቃ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

ጉባዔው ባስተላለፈው የደስታ መግለጫ መልዕክት፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ኅብረት ምሳሌ መሆኑን ገልጿል።

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን እና የጳጳሳት ጉባዔ ፕሬዚዳንት ከሐይማኖት አባቶች ጋር በመሆን በጉባ በተካሄደው የህዳሴ ግድብ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ መታደማቸውንም መጥቀሱን ኢዜአ ዘግቧል።

ላለፉት በርካታ ዓመታት በግንባታ ላይ ቆይቶ ትናንት ለምረቃ የበቃው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለመላው ኢትዮጵያውያን ብሎም አፍሪካውያን የስኬት ምሳሌ መሆኑንም ነው ጉባዔው የገለጸው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review