የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኅብረተሰቡ በአዲስ ዓመት በዓል በገበያ ቦታዎች ከተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላለፈ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኅብረተሰቡ በአዲስ ዓመት በዓል በገበያ ቦታዎች ከተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ራሱን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላለፈ

AMN – ጳጉሜን 5/2017 ዓ.ም

በአዲስ ዓመት በዓል የተለያዩ ግብይቶች የሚፈጸሙ በመሆኑ በገበያ ቦታዎች ህብረተሰቡ ከተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ራሱን እንዲጠብቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ አሳስበዋል።

ህብረተሰቡ በገበያ ቦታዎች ሲገበያይ በተለይም በገንዘብ ዝውውር ወቅት ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶች መጠቀም እና በተለይም በዲጂታል የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ላይ የተለየ ጥንቃቄ በማድረግ ከሚጠቀምበት ባንክ የሚደርሰውን መልዕክት በአግባቡ መመልከት እንደሚኖርበት ሃላፊው ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም አጭበርባሪዎች ስክሪን ሾቶችን በማሳየትና ተመሳስለው የተዘጋጁ የባንክ አፕሊኬሽኖችን በመጠቀም ከባንክ የተላከ አስመስለው የተለያዩ የማጭበርበሪያ መንገዶችን እየተጠቀሙ መሆኑን ፖሊስ የደረሰበት ስለሆነ ህብረተሰቡ በመሰል ድርጊቶች እንዳይታለል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ማሳሰባቸውን ጠቅላይ መምሪያው ለኤ ኤም ኤን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

በተጨማሪም ምግብ ነክ ነገሮችን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ለገበያ የሚያቀርቡ አንዳንድ ነጋዴዎች ስላሉ በግብይት ወቅት ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ያነሱት አቶ ሙሊሳ አብዲሳ፤ ድርጊቶቹ ከሰው ጤና ጋር በቀጥታ የሚገናኙ በመሆናቸው ማንኛውም ነጋዴ ለህብረተሰቡ የሚያቀርበው ምርት ጥራቱን የጠበቀ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ይህንን ሕገ-ወጥ ተግባር በሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይም ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ማመላከታቸው ተገልጿል።

ኅብረተሰቡ ማንኛውንም አጠራጣሪ ነገር ሲገጥመው በEFPapp፣ በ991 እና በማህበራዊ ገጾች ጥቆማዎችን እንዲሰጥና በተሰጠው ጥቆማ መሠረት ፖሊስ በቦታው በፍጥነት ደርሶ መረጃዎችንና ማስረጃዎችን በማሰባሰብ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድም በመግለጫው ተካቷል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመላው የሀገራችን ሕዝብ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review