ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዲሱ አመት ዋዜማ በአስራ ሶስት ተቋማት አንድ መቶ ሰባት የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶችን የሚሰጠውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከልን መመልከታቸዉን ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት የዘንድሮውን ዘመን ስናበቃ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ መሆኑን ለማረጋገጥ የነበረን ቁርጠኝነት እንደቀጠለ ነው ብለዋል፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከፌደራል አገልግሎቶች ወደ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እየተስፋፋ ይገኛል።
በአዲሱ አመት ዋዜማ በአስራ ሶስት ተቋማት አንድ መቶ ሰባት የከተማ አስተዳደር አገልግሎቶችን የሚሰጠውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ተመልክተናል ብለዋል፡፡
ይኽ አገልግሎት አሰጣጥን የመልካም አስተዳደር የድንጋይ ማዕዘን የማድረግ እና ዜጎች ወቅቱን የጠበቀ፣ ግልጽ እና ተደራሽ አገልግሎት የማረጋገጥ ቁርጠኝነታችንን የሚያንፀባርቅ ነው።
በአዲሱ አመት ገና ብዙ ማዕከላት ይኖሩናል። በድጋሚ መልካም አዲስ አመት ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡