በፊፋ ምዘና የተደረገለት የሀላባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም መጫወቻ ሜዳ ውጤት በሁለት ሳምንት ውስጥ ይታወቃል

You are currently viewing በፊፋ ምዘና የተደረገለት የሀላባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም መጫወቻ ሜዳ ውጤት በሁለት ሳምንት ውስጥ ይታወቃል

AMN- ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም

ህዝቡን በማስተባበር እየተገነባ የሚገኘው የሀላባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የመጫወቻ ሜዳው የፊፋ ባለሞያ ምዘና ተደርጎለታል፡፡

ግንባታው በጥሩ መንገድ እየሄደ ያለው ስታዲየም የተደረገለትን ምዘና ካለፈ ከድሬዳዋ በመቀጠል መጫወቻ ሜዳው ዓለም አቀፍ መመዘኛውን ያሟላ ሁለተኛው ስታዲየም መሆን ይችላል፡፡

ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው የታን ኢንጂነሪንግ ሃላፊ ፎዓድ ኢብራሂም ስታዲየሙ እየተገነባ ባለበት ሂደት ደስተኛ መሆናቸውን ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

የሀላባ መጫወቻ ሜዳ ምዘና ያደረጉት ከእንግሊዝ የመጡ በፊፋ እውቅና ያላቸው ባለሞያዎች እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

ባለሞያዎቹ ባዩት ነገር ደስተኛ እንደሆኑ እና የሜዳው ምዘና ሙሉ መረጃ ለፊፋ ላብራቶሪ መላኩን የታን ኢንጂነሪንግ ሃላፊ ፎዓድ ኢብራሂም ተናግረዋል፡፡ የምዘና ውጤቱም በሁለት ሳምንት ውስጥ እንደሚታወቅ አረጋግጠዋል፡፡

የሀላባ ስታዲየም በዋነኛነት በሀላባ ልማት ማህበር አስተባባሪነት ከህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከመጫወቻ ሜዳው ውጪ ዙሪያው በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሞያዊ ድጋፍ ተደርጎለት ዲዛይኑ ተጠናቆ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

የቀድሞ የዋልያዎቹ ተጫዋች የታን ኢንጂነሪንግ ሃላፊ ፎዓድ ኢብራሂም በቀጣይ የሀገራችንን የመጫወቻ ሜዳ ችግርን ለመፍታት በርካታ እቅዶች አሉን ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የሀላባ ስታዲየም ግንባታ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review