አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የ2018 ዓ.ም ዋዜማን በተለያዩ መርሃ ግብሮች በአራዳ ፖርክ በማክበር ላይ ይገኛል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፤ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፡ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የተለያዩ የሀይማኖች አባቶች ፤ አባ ገዳዎች ፡ የኤኤምኤን አመራርና ሰራተኞ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ሚኒስትሮች፤ አምባሳደሮች፤ ዲፕሎማቶች፤ የዉጪ ሃገር ዜጎች፤ የዳያስፓራ አባላት፤ ባለሃብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት፤ አትሌቶች፤ አርቲስቶችና ሌሎች የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችም በመርሃ ግብሩ ላይ ታድመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርሃ ግብሩ ላይ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡:
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት ጋር በመሆን ባዘጋጀዉ የበአል ዋዜማ ዝግጅት በኤኤምኤን ቴሌቪዥን፤ ኤኤምኤን ፕላስ ፤ በሬድዮ እንዲሁም በሁሉም የዲጂታል ሚዲያ አማራጮች በቀጥታ ለአድማጭ ተመልካቾቹ በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡
በበአል ዋዜማዉ ላይ የተለያዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች በመቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
በአስማረ መኮንን