የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአገራቸዉ ዉለታ ከዋሉ አረጋዉያን ፣ የአካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች መአድ ማጋራታቸውን ገልፀዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ወትሮም እንደምናደርገዉ አዲስ አመትን በከተማችን በሚገኙ 26 የምገባ ማዕከላት ጧሪ ፣ ደጋፊ ከሌላቸዉ አቅመ ደካምች ፣ በጉብዝናቸዉ ወራት ለአገራቸዉ ዉለታ ከዋሉ አረጋዉያን ፣ የአካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ከሆኑ ወገኖቻችን ጋር መአድ በማጋራት አሳልፈናል” ብለዋል፡፡
ከንቲባዋ የአዲስ አመት መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡