በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበበ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ማእድ አጋርተዋል ።
ሃላፊው በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 በሚገኘው 18ኛው የተስፋ ብርሐን የምገባ ማእከል ተገኝተው ማእድ አጋርተዋል።
ኢትዮጵያ ብዙ የአብሮነት እሴት ያለባት ሐገር ናት ያሉት አቶ ሞገስ ባልቻ ሐገርን በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ አሻግረው ለዚህ ትውልድ ላስረከቡ እናትና አባቶች በደከሙ ጊዜ አብሮነትና አጋርነትን በማሳየት ምርኩዝ መሆን ይገባል ብለዋል።
መሰል አጋርነትን የሚያሳዩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ያሉት ኃላፊው ኢትዮጵያውያን የአብሮነት እሴቶቻችንን ተጠቅመን ከየትኛውም የውጪ አካል እርዳታ በጋራ ሰርተንና ተደጋግፈን የሐገረን ብልጽግና ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።
በሄኖክ ዘነበ