በአዲስ አመት በደልን በይቅርታ ትቶ በሀገራዊ ጉዳይ በጋራ መቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት አሳሰበ

You are currently viewing በአዲስ አመት በደልን በይቅርታ ትቶ በሀገራዊ ጉዳይ በጋራ መቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት አሳሰበ

AMN-መስከረም 1/2018

በኢትዮጵያውያን ሀብት እና ጥረት የተጠናቀቀውን ሕዳሴ ግድብን የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት 50ኛ አመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ የምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዝዳንት ፓስተር ፃዲቁ አብዱ በየጊዜው እና በየዘመናቱ ለሀገራችን መሪዎች ጸልየናል ሁሌም እንጸልያለን ሲሉ በማንሳት ፣ የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን የጋራ ሀብታችን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አዲሱ አመት የአብሮነት እና የአንድነት አመት እንዲሆንም የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት ፕረዚዳንት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አክለውም በ2018 አዲስ አመት በደልን በይቅርታ ትቶ በሀገራዊ ጉዳይ በጋራ መቆም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት አሳሰበ

በምስጋና መርሃ ግብሩ ቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና የህዳሴ ግድብን በቅብብሎሽ ለፍጻሜ ላደረሱ የሀገር መሪዎችም ምስጋና አቅርበዋል ።

በ2018 አዲስ አመት በደልን በይቅርታ ትቶ በሀገራዊ ጉዳይ በጋራ መቆም እንደሚገባም እና ቀሪ የቤት ስራ አለብን ሲሉ ቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና በንግግራቸው ጠቅሰዋል፡፡

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review