የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ታላቁ የኢትዮጵያ ህደሴ ግድብ ግንባታ እውን እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዲስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገልጸዋል፡፡
አቶ ጃንጥራር አባይ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በአስመልክቶ ” በህብረት ችለናል ” በሚል መሪ ቃል በመስቀል አደባባይ በተካሄደዉ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ላይ እንደገለጹት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኢኮኖሚ ጥቅሙ ባሻገር በማኅራዊ ግንኙነት ህዝቡን ያስተሳሰረ የጋራ ሀብት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመላው ኢትዮጵያዊያን ተሳትፎ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በድምቀት መመረቁን ያነሱት አቶ ጃንጥራር፣ ይህ ትልቅ ስኬት ከእናቶች መቀነት እስከ ትላልቅ ባለሀብቶች ገንዘብ አዋጥተው እውን ያደረጉት ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችም የታላቁ ህደሴ ግድብ ግንባታ እውን እንዲሆን ባለፉት 14 አመታት ሰፊ ጥረት አድረገዋል ብለዋል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ህልማችንን በጋራ ያሳካንበት ፕሮጀክት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ወጣቶች የስፖርት ቤተሰቦች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል፡፡
በአስማረ መኮንን