የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ መመረቁን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ ለሚደረገው የድጋፍ ሰልፍ የተወሰኑ መንገዶች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
በትውልድ ቅብብሎሽ ዕውን የሆነው የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጳግሜ 4 ቀን 2017 ዓ/ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ( ዶ/ር) በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት መመረቁ የሚታወቅ ነው።
ከምረቃው ዕለት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተካሄዱ ሲሆን ዕሁድ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ የተዘጋጀ ሲሆን መርሀ ግብሩን ምክንያት በማድረግ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት በከተማው የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል ፡፡
በዚህም መሠረት ከመስከረም 3 ቀን 2018 ዓ/ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ የድጋፍ ሰልፉ እስከሚያልቅ ድረስ የሚከተሉት መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ማቆም እንዲሁም ዝግ ይደረጋሉ፡-
– ከልደታ ፍርድ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
– ከአትላስ ወደ ቅዱስ ዑራኤል ፒኮክ መብራት ላይ
– ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ጠማማ ፎቅ ላይ
– ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መስቀለኛ ላይ )
-ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
– ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ላይ)
– ከሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቲያትር ጎማ ቁጠባ መብራት ላይ
– ከተክለ ኃይማኖት አደባባይ በኢምግሬሽን ጥቁር አንበሳ ላይ
– ከንግድ ማተሚያ ወደ ፍልውሃ ንግድ ማተሚያ መስቀለኛ ላይ
– ከቸርችል ወደ ጥቁር አንበሳ መብራት ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ
– ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ፓርላማ መብራት
– ከሀራምቤ መብራት ወደ ሳንጆሴፍ መብራት ሀራምቤ መብራት ላይ
– ከብሔራዊ ቲያትር ወደ ለገሀር መብራት
– ከሰንጋ ተራ 40/60 ወደ ለገሃር ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ ላይ
– ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት ሜክሲኮ አደባባይ ላይ
– ከአረቄ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ አረቄ ፋብሪካ መስቀለኛ ላይ
– ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ባልቻ ሆስፒታል መታጠፊያ ላይ
– ከቫቲካን ኤምባሲ ወደ ሳር ቤት አደባባይ ሳር ቤት አደባባይ ላይ
– ከቅዱስ ዮሴፍ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ
– ከቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር ቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መብራት ላይ መንገዶቹ የሚዘጉ ሲሆን በተጠቀሱት መስመሮች ላይ ከዛሬ መስከረም 3 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽት 12፡00 ሠዓት ጀምሮ ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡