በአዲስ አበባ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing በአዲስ አበባ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

AMN – መስከረም 4/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ፣ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ታድመዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የማንሰራራት ዘመን ጅማሮ፣ የመደመር አሻራ ብሎም የወል ድል ማሳያ በትውልድ ቅብብሎሽ ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ በቅቷል።

የኢትዮጵያውያን የአዲስ አመት ስጦታ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በርካቶች በላባቸውና በደማቸው መስዋዕትነትን ጭምር ከፍለው ለድል አብቅተውታል።

ከግድቡ ግንባታ ጅማሮ አንስቶ እስከ ፍፃሜው መላው ኢትዮጵያውያን በተባበረ ክንድ አሻራቸውን አኑረው ዛሬ በጋራ ደስታቸውን እያከበሩ ይገኛሉ።

ለምሽቱ ድቅድቅ ጨለማ እጅ አንሰጠም ያሉ የመዲናዋ ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው የድሉን ፍሬ በህብረት እያጣጣሙ ይገኛሉ።

በተለያዩ ባህላዊ አልባሳትና መፈክሮች የታጀበው የመዲናዋ ትዕይንተ ህዝብ እንደቀጠ ይገኛል።

በሚካኤል ሕሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review