ኪነ ጥበብ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ውስጥ አበርክቶው የጎላ እንደነበር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ኪነ ጥበብ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ውስጥ አበርክቶው የጎላ እንደነበር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) ገለጹ

AMN – መስከረም 4/2018 ዓ.ም

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ “ሚስ ህዳሴ” በሚል የቁንጅና ውድድርና የኪነ ጥበብ መድረክ እየተካሔደ ነው።

መድረኩ በዋናነት ከአደዋ ድል ቀጥሎ የወል ታሪካችን የሆነው ታላቁ ህዳሴ ግድብን መሆኑ በትውልድ ልብ ውስጥ ማኖር የመድረኩ አላማ እንደሆነ የአዲስ አበባ ባህልና ኪነ ጥበብ ቢሮ ኃላፊ ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የህዳሴ ግድብ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የብሔራዊ ትርክት ግንባታችን መሰረት፣ የኢትዮጵያውያን የአንድነት ትእምርት ነው ያሉት ሒሩት (ዶ/ር)፣ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ውስጥ ቁጭትን ከመፍጠር ጀምሮ ህዝብን በአንድነት በማስተባበር ሒደት ኪነ ጥበብ አበርክቶው የጎላ ነበር ብለዋል።

አሁን ከዘመናት ቁጭት ተላቀን፣ በብዙ ውጣ ውረድና ልፋት ውስጥ አልፈን ድላችንን እያጣጣምን ነው፣ ይህንን ብዙ ትርጉም ያለው የድል ስኬታችንን በተለያዩ የኪነ ጥበባዊ ስራዎች በትውልድ ውስጥ ማስረጽ ያስፈልጋልም ብለዋል።

በህዳሴ ግድብ የታየውን መተባበርና አንድነትን በማስቀጠል ብሎም ብሔራዊነትን በማጽናት በሌሎች የሐገር ግንባታ ውስጥ የመድገም ስራ ላይ በትኩረት እንደሚሰራም ሒሩት (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review