በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገበዉ የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ስኬት ለቀጣይ የትምህርቱ ዘርፍ ዉጤታማነት መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
የ2017 የ12ኛ ክፍል ዉጤትን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስትር መግለጫን ሰጥቷል፡፡
በዚህም አዲስ አበባ ከተማ 28.9 በመቶ ተማሪዎችን በማሳለፍ አንደኛ ደረጃን ተቆናጣለች፡፡ ሀረሪ እና አማራ ክልል 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታን ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/)፣ በመዲናዋ በትምህርቱ መስክ የተገኘዉ ስኬት ለቀጣይ ስራዎች ምቹ መደላድል የሚፈጥር ነዉ ብለዋል፡፡
ተማሪዎችን በማሳለፍ ምጣኔ ከፍተኛ ዉጤቶችን በብዛት በማስመዝገብ እና በመሰል መለኪያዎች በ12ኛ ክፍል ዘንድሮ የታየዉ ለዉጥ ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርቱ ዘርፍ የሰጠዉን ትኩረት ያሳየ ነዉ ብለዋል፡፡
የተማሪዎች መገባ፣ የትምህርት ቤቶች ደረጃ መሻሻል፣ የመምህራን የአቅም ግንባታ ስራ እና የወላጆች ቅንጅታዊ ስራ ለተገኙ ስኬቶች መነሻ ናቸዉ ያሉት ዘላለም (ዶ/ር) በቀጣይም መሰል ተግባራት ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
በተመስገን ይመር
#Education
#Addisababa